የ40 40 20 ቀመር በድሬዳዋ እና መዘዙ

በአማኑኤል ታደሰ

በ1996 ዓ.ም ላይ በቻርተር ደረጃ ከተመሰረቱት ሁለት የኢትዮጵያ ከተሞች የምስራቅ ኢትዮጵያዋ ድሬዳዋ ከተማ አንዷ ነች፡፡ ከተማዋ በ9 የከተማ ቀበሌዎች እና በ38 የገጠር ቀበሌዎች የተዋቀረች ናት፡፡ በ1999 ዓ.ም የሀገር አቀፍ የህዝቦችና ቤቶች ቆጠራ ኮሚሽን ባጠናከረው የህዝብ ቆጠራ መረጃ መሰረት የድሬዳዋ ህዝብ ብዛት ወደ 341 ̦834 እንደሚደርስ ይገመታል፡፡ በ39 የድሬዳዋ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩት የህዝብ ብዛት ስንመለከት ወደ 108̦̦̦ 610 እንደሚደርስ ይገመታል፡፡ በዘጠኙ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው የከተማው ህዝብ ብዛት ቢያንስ ወደ 233̦ 224 ይደርሳል፡፡ በከተማዋ ከሚኖሩ ህዝቦች ኦሮሞ 33 ፐርሰንት አማራ 29.5 ፕርሰንት ሶማሌ 23.5 ፐርሰንት ጉራጌ 6.7 ፐርሰንት፤ ትግራዋይ 1.8 ፐርሰንት፤ ሀረሪ 1.6 ፐርሰንት እና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት የህዝቡ ቁጥር ወደ 500̦ 000 እንደሚደርስ ይገመታል፡፡ ድሬዳዋ በሀገራችን ከሚገኙ የኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ የብዙ ብሄር ብሄረሰብ እና ህዝቦች (Multi-Ethnicity) መገኛ የሆነች፤ በፍቅር እና በመቻቻል የሚኖሩባት ከተማ ነች፡፡ ከተማዋ የኢትዮ-ጂቡቲን የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ትስስሩን ለማሳለጥ ይረዳ ዘንድ እንደ ስተራጂካዊ ቦታ ተደርጋ ትወሰዳለች፡፡ በጂቡቲ በኩል ለሚደረጉ የወጪ እና የገቢ ንግድ ትስስሮችም ዋነኛ ማሳለጫ ከተማ ናት፡፡ ከተማዋ በሌሎች የሀገሪቷ ህዝቦች ዘንድ በንግድ እና በኢንዱስትሪ መናኸሪያነቷ ትታወቅ እንደነበረች ከዚያ ለጥቆም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ከተሞች ውስጥ በእድገት ከአዲስ አበባ ቀጥላ ትመደብ እንደነበረች ከታሪክ ማህደሯ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ነገር ግን የያኔው የእድገት ፍጥነቷ ብሎም የያኔው ትልቅ ስሟ ዛሬ አብሯት ያለ አይመስልም ወይንም እየደበዘዘ መጥቷል ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡ ለማነፃፀሪያ እንኳን ከድሬዳዋ ባነሰ እድሜ ክልል ላይ የምትገኘው የሀዋሳ ከተማ እንኳን ብንመለከት በምን ያህል የኢኮኖሚ እድገት እና ፍጥነት (Economic Development Pace) ላይ እንደምትገኝ ለመመስከር የUNDP አልያም የማዕከላዊ ስታስቲክ ኮሚሽን ዓመታዊ ሪፖርትን መቃረም ሳያስፈልግ መረዳት የሚቻል ይመስለኛል፡፡ ከሚታዩት አንዳንድ የብልጭታ ለውጦች በስተቀር የነበራት መሰረተ ልማቶች ድሮም የነበሩ ናቸው፡፡ ተጀምረው በጅምር ብቻ የቀሩ መሰረተ ልማቶችንም እንዲሁ በከተማዋ መታዘብ ይቻላል ለምሳሌ የድሬዳዋ አዲሱ የድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ተጠቃሽ ማስረጃ ሊሆነን ይችላል፡፡ ይህ ማለት በአጭሩ የከተማዋ ህብረተሰብ እና ተወላጆች ለብዙ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ብሎም ፖለቲካዊ ችግሮች ከተጋለጡ ሰንበትበት ብለዋል፡፡
የፖለቲካዊ ጉዳዮቿን ስንመለከት በሽግግር መንግስት ምስረታ ወቅት በወጣው ኣዋጅ ቁጥር 7/1983 መሰረት ከተማዋ ትደዳደር የነበረው ከማዕከላዊ መንግስቱ በሚመደብላት አስተዳዳሪ ነበር፡፡ አስከ ቅርብ ጊዜም ጭምር ማለት ነው፡፡ ከሽግግር መንግስት ምስረታ ማግስት ማለትም ከህዳር 1983 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 1985 ዓ.ም ድረስ ያስተዳደሯት የቀድሞ የኦህዴድ/ኢህአዴግ አባል የነበሩት አቶ ሀብታሙ አሰፋ ዋቅጅራ ነበር፡፡  እንደሚታወቀው ሁለቱ ብሄሮች ማለትም የሶማሌ ኢሳ ጎሳ እና በኦሮሞ ብሄረሰቦች ዘንድ ደግሞ የጉርጉራ ጎሳዎች በድሬዳዋ ከተማ ላይ የባለቤትነት ጥያቄዎች ያነሳሉ፡፡ በዚህ ልዩነቶች ምክኒያት ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት በማሰብ ይመስላል የፌዴራል መንግስቱ በአዋጅ ቁጥር 7/1984 መሰረት ከተማዋን ‹‹ጊዜያዊ አስተዳደር›› በሚል በእርሱ ስር እንድትሆን አደረገ፡፡ በተጨማሪም ሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም የሶህዴፓ እና የኦህዴድ ፓርቲዎች የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻላቸው ከሁለቱ ውጪ የሆነ ሰው ‹‹አስተዳዳሪ›› ከፌዴራል መንግስቱ እየተሾመላት እንድትቆይ ተደረገች፡፡ በዚህ ምክኒያት ከ1987 ዓ.ም እስከ 1995 ዓ.ም ድረስ የአማራ ተወላጅ በነበሩት አቶ ሰለሞን ሀይሉ በሊቀ-መንበርነት እንዲመሯት ተደረገ፡፡ እንደሚታወቀው እስከ 1995 ዓ.ም ድረስ ከተማዋ በሊቀ/መንበር ነበር የምትመራው፡፡
ከ1996 ዓ.ም በኋላ በአዋጅ ቁጥር 416/1996 መሰረት ድሬዳዋ ‹‹ከጊዜያዊ የፖለቲካ አስተዳደርነት›› ወደ ‹‹ሙሉ የከተማ ፖለቲካዊ አስተዳደርነት›› ተቀይራ ‹‹የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር›› ማለትም ወይንም የቻርተር ከተማ ሆና መጠራት ጀመረች፡፡ ከ1996 ዓ.ም እስከ 1998 ዓ.ም ድረስ ከተማዋን በዋና አስተዳዳሪነት የቀድሞው የህወሃት ነባር ታጋዩ አቶ ፍስሀ ዘሪሁን (መአሲ) በአቶ አባይ ፀሀዬ ተሹመው አገልግለዋል፡፡ ከ1998 እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ ደግሞ በፌዴራል መንግስቱ ተመድበው አቶ አብዱላዚዝ ሞሀመድ ድሬዳዋን አስተዳድረዋል፡፡
ከሽግግሩ መንግስት ምስረታ ማግስት ጀምሮ እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ የድሬዳዋ ከተማ በፌዴራሉ መንግስት ስር ስትታሽ ከርማለች ነገር ግን ድሬዳዋ ከፌዴራል መንግስቱ መዳፍ ስር ሊያወጣት የሚያስችላትን የእራሷን 300 መቀመጫ ያለው አዲስ ም/ቤት በ2000 ዓ.ም አቋቋመች፡፡ የምክር-ቤት አባሎቿን ደግሞ በሚያዚያ 12 2000 በተካሄደ ምርጫ አማካኝነት አሟላች፡፡ የከተማዋ መንግስት የሚመሰረተው በሁለቱ ጥምር ፓርቲዎች ውህድ ማለትም በኦህዴድ እና በሶህዴፓ ነው፡፡
አዲሱ ም/ቤትም በሰኔ 13 2000 ዓ.ም አቶ አደም ፋራሃን በህዝቡ የተመረጡ የመጀመሪያው ከንቲባ አድርጎ ሾማቸው፡፡ በነገራችን ላይ ከተማዋ በከንቲባ መተዳደር የጀመረችውም ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ አቶ አደም ፋራሃ ከተመረጡበት ወርሃ ሰኔ 13 2000 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ በከንቲባነት ከተማዋን መርተዋል፡፡ እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት አንቀፅ 46 መሰረት ሀገራችን ኢትዮጵያ ዘጠኝ ክልሎች እና ሁለት የከተማ መስተዳደሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ እነዚህም የከተማ መስተዳደሮች የሀገሪቷ ዋና መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ ስትሆን ሌላኛው ከተማ ደግሞ ድሬዳዋ ናት፡፡ በህገ-መንግስቱ ከድሬዳዋ በስተቀር ሁሉም የሀገሪቷ ክልሎች እና አዲስ አበባ በአንቀፅ 49 መሰረት ህገ-መንግሰታዊ እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ድሬዳዋ ግን ህገ-መንግስታዊ እውቅና ተነፍጋለች፡፡ ይልቅ በአዋጅ መሰረት የፌዴራል ከተማ ሆና ተዋቅራለች፡፡ ይህ ህገ-መንግሰታዊ እውቅና ለሌሎቹ ክልሎች እራስን በእራስ የማስተዳደር መብትን አጎናፅፏቸዋል በአንቀፅ 39 መሰረት ማለት ነው፡፡ ከዚህ ህገ-መንግስታዊ ትርጓሜ መረዳት የምንችለው ደግሞ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እራሳቸውን በእራሳቸው የማስተዳደር መብት እንዳላቸው በግልፅ ይደነግጋል፡፡ በምሳሌ ብናየው የትግራይ ክልልን የኦሮሚያ ተወላጆች በምንም መመዘኛ ሊያስተዳድረው አይችልም፡፡ የትግራይ ክልልን ሊያስተዳድር እና ሊመራ የሚችለው የትግራይ ተወላጅ ነው ማለት ነው፡፡ ምክኒያቱም ህገ-መንግስቱ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች እራሳቸውን በእራሳቸው የማስተዳደር መብት ስለሚያጎናፅፋቸው፡፡ ሌላው የድሬዳዋ ከተማ እንደሚታወቀው የብዙ ብሄር ብሄረሰብ መኖሪያ እና የCosmopolitan City እንደመሆኗ መጠን መተዳደር ያለባት በከተማዋ ህበረተሰብ ነው፡፡ ያማለት ሁሉም በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩ ህብረተሰብ እኩል አለምንም ልዩነት እራሳቸውን በእራሳቸው የማስተዳደር መብት አለምንም የብሄር የሀይማኖት የዘር እና የመደብ ልዩነት ሳይኖር በተግባር ሊጎናፀፉ ይገባል፡፡ ነገር ግን በከተማዋ በተለይ ፖለቲካዊ ስልጣኖች ወይንም የምክርቤት አባላት ወንበር እንኳን የሚያዘው በህግ ባልተደገፈው የ40፡40፡20 ቀመር ነው፡፡ ይህ ቀመር ተግባራዊ መደረግ የጀመረው የከተማዋን ደህንነት እና የሁለቱን ብሄር የስልጣን ሽኩቻ ለማስታመም በሚል በሁለቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ስምምነት ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡
የከተማዋ የፖለቲካ የስልጣን ክፍፍሉ በሚገርም ሁኔታ የሚቀየደው የአንድ የእግር ኳስ ጨዋታ አሰላለፍ በሚመስል መልኩ ነው፡፡ በተለምዶ የእግር ኳስ ኢሊቶች የሚጠሩት የአሰላለፍ አይነት በሆነው 4፡4፡2 አይነት ቀመር ነው፡፡ ይህንን ቀመር ግልፅ ለማድረግ 40 ፐርሰንት ለኦሮሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) እንደገና 40 ፐርሰንት በተለምዶ አጋር ፓርቲ ተብሎ ለሚጠራው የሶማሌ ህዝቦች ዴሞክረሲያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ) ቀሪው 20 ፐርሰንት ደግሞ ለቀሪዎቹ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ህዝብ (ኢህአዴግ) እህት ድርጅቶች የሚከፋፈል ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ ቀመር ምንም አይነት የህግ ድጋፍ የሌለው የአፓርታይድ ቀመር ነው ማለት ይቻላል፡፡ የአፓርታይድ ቀመር ይመስላል ያልኩበት ምክኒያት ለምሳሌ ዛሬ ደቡብ አፍሪካ ለሎች የአፍሪካ ሀገራት የዲሞክራሲ ምሳሌ ተደርጋ ከመወሰዷ በፊት የአፓርታይድ ስርዓት አይሎ እንደነበረ ከሶዌቶዋ ታሪክ ማገላበጥ ይቻላል፡፡ እንደሚታወቀው በደቡብ አፍሪካ ነጭ ጥቁር በሚባል የዘር መመዘኛ ጥቁሮች ይበልጡንም የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ በደሎች ይደርሱባቸው ነበር፡፡ በድሬዳዋ ከተማ ያለው 4፡4፡2 የቀመር መመዘኛ ከደቡብ አፍሪካው የሚለየው መሰረቱን ብሄር ላይ ማድረጉ ነው፡፡ ከተማዋን ከስር መሰረቷ የብዙ ብሄር ብሄረሰብ መኖሪያ እና የፌዴራል ከተማ መሆኗ እየታወቀ የሁለቱን ብሄር ኤሊቶች የፖለቲካ ፍላጎት እና የፌዴራል መንግስቱን ፍላጎት ብቻ ለመጥቀም ታስቦ ሌሎች ብሄሮችን ከጨዋታ ውጪ ማድረግ እና ከተማዋን የሚጠበቅባትን እድገት እንዳታገኝ አድርጓታል፡፡ የከተማው ህብረተሰብም በዚህ ቀመር የሚገባውን የኢኮኖሚ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ግልጋሎቶችን በተገቢው ፍጥነት እና ጊዜ ማግኘት እየቻሉ አይደለም፡፡ ይህንን የሚደግፍ እንድ ማስረጃ ለማግኘት እሩቅ መሄድ ሳያስፈልገን የቀድሞ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር ዲኤታ የነበረው እና የአሁኑ የኢሳት ቋሚ የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው በመስራት ላይ የሚገኙት ‹‹አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ›› የስርዓቱን ገመና አደባባይ ባወጡበት ‹‹የመለስ ትሩፋቶች (ባለቤት አልባ ከተማ)›› በሚለው መፅሀፋቸው በገፅ 17 ላይ ስለ ድሬዳዋ እንዳሰፈረው ‹‹ድሬዳዋን ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በስርዓቱ ሌላኛዋ የፖለቲካ ቁማር እና ሸፍጥ የተሰራባት ከተማ ናት ይላታል፡፡››
ድሬዳዋ ከተማ በዚህ ቀመር ምክኒያት በፌዴራል መንግስቱ ስር ሆና የብሄር ብሄረሰቦች ከተማም ጭምር ሆና ከተማዋ የዋና እና የምክትል ከንቲባ ቦታዎች በሁለቱ ብሄሮች ይያዛሉ፡፡ አብላጫው የምክር ቤት መቀመጫዎችም የሚያዙትም ሁለቱን ብሄር በሚወክሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነው፡፡ የአስፈፃሚው አካላት ቦታዎችም በዚሁ 40፡40፡20 መመዘኛ ይከፋፈላሉ፡፡ ሌላው እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ የምርጫ ስነ ስርዓት ህግ ምርጫ በየአምስት ዓመት አንዴ ይካሄዳል፡፡ ያሸነፈው የፖለቲካ ፓርቲም አምስት ዓመት ያስተዳድራል ማለት ነው፡፡ እናም እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች ባሸነፉበት ምርጫ አምስት ዓመቱን ለሁለት እንደ ቅርጫ ይካፈሉት እና ሁለት ዓመት ከግማሽ ሁለት ዓመት ከግማሽ ያስተዳድሯታል፡፡ በሌላ አነጋገር ሶህዴፓ የመጀመሪያዎቹን ሁለት ዓመት ከአምስት ወር ካገለገለ በኋላ ቀሪውን ሁለት ዓመት ተኩል ደግሞ ኦህዴድ ያስተዳድራል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በየሁለት ዓመት ተኩል የነበረው የስልጣን ጊዜ በየአምስት ዓመቱ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የድሬዳዋ ቻርተር አንቀፅ 23 ንዑስ አንቀፅ 2 ሐ እንደሚደነግገው የከተማዋ ስራ አስኪያጅ ሲሾም ‹‹ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች በቀበሌ ስራ አስኪያጅነት ይቀጥራል ይላል፡፡ ይህ ማለት አለምንም የቀመር መመዘኛ በግልፅ የስራ ብቃትን እና ችሎታን መሰረት ባደረገ መልኩ የቀበሌ ስራአስኪያጆች እንዲቀጥር ፈቃድ ይሰተዋል፡፡ በሌላ ቋንቋ ከፓርቲዎቹ ጋር ንክኪ የሌለው ሰው ሆኖ እውቀት እና ችሎታን መሰረት ባደረገ መመዘኛ ቅጥሩ ሊፈፀም እንደሚገባ ይደነግጋል፡፡ ይህም ማለት ፖለቲካ እና ሙያ ለየቅል ቅል ሆነው በከተማው ባሉት ቀበሌዎች ላይ ያሉ ስራ-አስኪያጆች መቀጠር እና መመረጥ ያለባቸው ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ መሆን እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ ነገር ግን በተግባር እየሆነ ያለው በዚህ 40፡40፡20 በሚለው ቀመር መሰረት የሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲ ግለሰቦች እየተፈራረቁ የከተማዋን የስራ-አስኪያጅ ቦታዎች በፓርቲዎቻቸው ካድሬዎች ይዘውሩታል፡፡ በነገራችን ላይ በሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችም ጭምር ማለትም በብአዴን በህወሃት እና በደኢህዴን ድርጅቶችም ጭምር ይህ ቀመር አይወደድም፡፡ በከተማው ተወላጅ እና ነዋሪዎችም ጭምር ዘንድ ተቀባይነቱ እያጣ የመጣ እና የማይወደድ ቀመር ነው፡፡ ለዚህም ነው የከተማው ነዋሪ እና ተወላጁ የ40፡40፡20 ቀመር እንዲወገድ እና ድሬዳዋ የሁሉም ቤት እንድትሆን እየተጋ ያለው፡፡

ድሬዳዋ ከተማን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ስርዓት ለየት የሚያደርጋት አስገራሚ ነገሮችን ታቅፋ እኖረች ትገኛለች፡፡ ከእነዚህም መሀከል የፌዴራል ከተማ ብሎም የብሄር ብሄረሰብ መኖሪያ ሆና ህገ-መንግስታዊ እውቅና የሌላት መሆኑ ለየት ያደርጋታል፡፡ እንደሚታወቀው የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 61 የፌዴሬሽን ም/ቤት በፌዴራል መንግስቱ አባል ክልሎች በሚወክሉአቸው አባላት እንደሚዋቀሩ ይደነግጋል፡፡ ነገር ግን እንደ አዲስ አበባ ሁሉ በፌዴሬሽን ምክር-ቤት ውክልና የሌላት ከተማም ናት፡፡ ሌላው የፌዴሬሽን ም/ቤት ህገ-መንግስት ከመተርጎም በተጨማሪ የበጀት ማከፋፈያ ቀመር በመስራት ለክልሎች ድጎማ ይሰጣል፡፡ ድሬዳዋ የክልልነት ስልጣን ስለሌላት በፌዴሬሽን ም/ቤት ልታገኝ የሚገባትን ወንበር አላገኘችም፡፡ ስለሆነም ክልል ባለመሆኗ ምክኒያት የፌዴሬሽን ምክር-ቤት በሚሰራው ህጋዊ የበጀት ቀመር ስሌት ውስጥ ተሳትፎ አታደርግም፡፡ ያማለት ሌሎች ክልሎች በበጀት የቀመር ስሌት ጉዳይ የመወሰን ስልጣን እንኳን የላትም፡፡
v የከተማዋን የእድገት ስንክሳር ካበዙት አበይት እና ዋነኛ ምክኒያቶች ውስጥ ዋነኛው የ40፡40፡20ው የአፓርታይድ ቀመር ነው፡፡ ይህ ቀመር ያስከተላቸውን ችግሮች አንድ በአንድ እንመልከታቸው፡፡
አንድ፡- ይህ የሁለት ዓመት ተኩል የፖለቲካ ስልጣን ክፍፍል የሚያስከትለው ዋነኛ ችግሩ አንድ አመራር ይመጣና በከተማዋ ላይ አዲስ ፖሊሲ እና የልማት ዕቅድ ይዞ ይመጣና በአግባቡ ሣይተገብረው የስልጣን ዘመኑ ያበቃል፡፡ ያማለት የሚፈልገውን ወይንም ከተማዋ የሚጠበቅባትን የኢኮኖሚ ለውጥ እና እድገት እንታመጣ ትልቅ ማነቆ ሆኗታል፡፡ በአጭሩ ጥሩ አመራር እና የተረጋጋ አመራር (stable leadership) የሌለባት ከተማ ናት ማለት ይቀላል፡፡ በዚህ ምክኒያት የማዘጋጃ ቤት ስራዎች በአግባቡ አይከወኑም፡፡
ሁለት፡- ከዚህም ባሻገር በከተማዋ የሁለቱን የፖለቲካ ኤሊቶች (ልሂቆች) በከተማዋ የፖለቲካ የበላይነትን ለመያዝ በሚያደርጉት ፖለቲካዊ ግብግብ በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩትን ብሄሮች ያገለለ ይሆናልም እያደረገ ያለ ሀቅ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ከተማዋ ላይ የሚፈልሰው ህዝብ ቁጥሩ በጣም እየጨመረ ነው ማለትም Demographic Change እያመጣ ነው ይህ ለውጥ ደግሞ በዘላቂነት መፍታት ካልተቻለ ከተማዋን ይበልጥ ለብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች ያጋልጣታል፡፡
ሶስት፡- የሁለቱን ድርጅቶች ፖለቲካዊ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት ሲባል ከተማዋ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ይበልጡኑ እንድትቸገር አድርጓታል፡፡ ከተማዋ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተተብትባ የዲሞክራሲያዊ መርሆች የማይከበሩባት ከተማ ወደ መሆን አየተሻገረች ነው፡፡ ይህ ቀመር ሁለቱ ድርጅቶች ወክለነዋል የሚሉትንም የህብረተሰብ ክፍል መጥቀም አልቻለም ይልቅ በሌላው የህብረተሰብ ክፍል በጥርጣሬ እንዲታይ እያደረገው ነው የሚገኘው፡፡
አራት፡- ይህ በኢህአዴግ ፓርቲዎች ውስጥም ወደፊት ሽኩቻን እና አለመተማመንን ሊፈጥር የሚችል ሀቅ መሆኑን መረዳትም ያስፈልጋል፡፡ የዚህ አለመተማመን ውጤት ይበልጥ ገፈት ቀማሽ የሚሆነው የከተማው ህዝብ ነው፡፡
አምስት፡- ከተማዋን ላለፉት ዓመታት እየተዳደረች የምትገኘው ከተማዋን ምንም በማያውቁ ከሌላ ቦታ የመጡ ይባስ ብሎ የከተማውን ሕዝብ ስነ-ልቦና ጭምር መረዳት የማይችሉ ናቸው፡፡ ከዚያም ባለፈ የህዝቡን እራስን በእራስ የማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ መብት የሚነፍግ ነው፡፡ አዋጅ ቁጥር 416/1996 በመግቢያው ላይ አዋጁ የተቋቋመበት ዓላማን ሲያብራራ እንደሚከተለው ይደነግጋል፡፡ ‹‹ይህ አዋጅ የተቋቋመበት ዓላማ ለድሬዳዋ ነዋሪ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ስልጣን ለመወሰን ነው ይላል፡፡›› ከዚህ ድንጋጌ መረዳት የሚቻለው የከተማው ህብረተሰብ እራሱን በእራሱ የማስተዳደር ስልጣን አለው ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ባለፉት ጊዜያት በከተማው የተስተዋለው ከዚህ በተፃፃራሪ ነው፡፡ ለምሳሌ እንኳን ብናነሳ የቀድሞው የከተማዋ ከንቲባ የነበሩት አቶ አብዱላዚዝ ሞሀመድ የመጡት ከሀረማያ ነው፡፡ የቀድሞው የከተማው ስ/አስኪጅ የነበሩት አቶ ባሀር አሜም የመጡት ከሀረማያ ነው፡፡ የቀድሞው ከንቲባ ሀሰን ዚያድም እንዲሁ የመጡት ከሂርና ነው፡፡ ድሬዳዋን ካስተዳደሩት አብዛኛውን ማለት ይቻላል ከአቶ አደም ፋራ በስተቀር ድሬዳዋ ተወልደው ድሬዳዋ ያላደጉ እና የህዝቡን ስነ-ልቦና የማያውቁ ናቸው፡፡ የአሁኑ የከተማዋ ከንቲባዋ አቶ ኢብራሂም ሁስማን በእርግጥ በቅርብ ለመሰናዶ ት/ት ተማሪዎች ልምዳቸውን ለማካፈል በተገኙበት መድረክ ላይ ሲናገሩ እንደሰማሁት ትውልድ እና እድገታቸው እዚሁ ከተማ ውስጥ መሆኑን ከአንደበታቸው ሰምተናል፡፡ የከተማዋን ስነ ልቦና እና ማህበራዊ መሰረት መረዳት የሚችል ሰው ታጥቶ ሳይሆን ፖለቲካዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ብቻ መሯሯጥ ስለሚቀናቸው እንጂ፡፡ ስለሆነም ከተማዋ የብሄር-ብሄረሰብ ከተማ እስከሆነች ድረስ ከተማዋን ለሁሉም ክፍት በማድርግ ህብረተሰቡ ከዚህ ከፋፋይ ቀመር ውጪ እራሳቸውን በእራሳቸው እንዲያስተዳድሩ መፍቀድ ይገባል፡፡
ስድስት ተሿሚዎቹ በተሾሙበት ዓመት እራሳቸውን እና በዙሪያቸው ያሉትን ግለሰቦች ጠቅመው ነው ከመንበራቸው የሚወርዱት፡፡ ከተማዋ በሙስና እንደምትታወቅ ለማንም ግልፅ ነው በተለይ ከመሬት ይዞታ እና ከተቋማት ግንባታ ጋር ተያይዞ የሚዘወተሩ ሙስናዎች መበራከት ለአብነት መውሰድ ይቻላል፡፡ ለዚህ ማሳያ ይሆነን ዘንድ ከቀድሞዎቹ የከተማዋ ባለስልጣኖች መሀከል ለምሳሌ የቀድሞው የድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ባህር አሜ ዛሬ የት እንደሚገኙ ማወቁ ብቻ በቂ ነው፡፡ እስቲ በየመንደሮቻቹ ያገለግሉ የነበሩ የቀበሌ አመራሮቹን መመልከትም ይቻላል፡፡ ግማሹ አመራሮች ከብቃት ማነስ እና ብልሹ የመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ በህዝብ ጩኸት ከአንድ ቀበሌ ይነሱና ሌላኛው ቀበሌ ሲሾሙ ታያለህ፡፡ ሌላው ደግሞ ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉ አመራሮች በሰሩት ወንጀል ሣይጠየቁ በደፈናው የወሰዱትን ወይንም የዘረፉትን ወስደው ከህዝቡ ገሸሽ እንዲሉ ይደረጋል፡፡
ሰባት ሌላው ከድንበር ማካለል ጋር ተያይዞ ከተማዋ ችግሮች አሉባት፡፡ ለምሳሌ በድሬዳዋ እና በሽንሌ ዞን መካከል የድንበር ማካለል ጥያቄዎች አሉ እነዚህም እችግሮች ተቀርፈው እልባት ሊያገኙ ይገባል፡፡ ለምሳሌ ዛሬ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሰፈረበት ቦታ እንኳን አንዱ መከራከሪያቸው ነው ከሌሎች ግንባታዎች በተጨማሪም ማለት ነው፡፡
ስምንት ከተማዋ በዚህ ቀመር ተተብትባ የስራ እድሎች በቅጡ የማይፈጠርባት ከተማ ሆናለች፡፡ የተፈጠሩትም ትንሸ የስራ ዕድሎች እንኳ በፍትሀዊነት ህጉን መሰረት ባደረገ መልኩ ለስራ አጡ ማህበረሰብ በአግባቡ አይደርስም፡፡ በዚህም ምክኒያት የስራ አጥ ቁጥሩ ይበልጡኑ እየተንሰራፋ ሄዶ አብዛኛውን ወጣት ቀዩውን ለቆ ለስደት እና ለእንግልት እየተዳረገ ስለመሆኑ ብዙ ማሳያዎቹን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እንደ ድሬዳዋ የከተማ ስራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በ2008 እና በ2009 ዓመት በጀት ባስጠናው ጥናት መሰረት የከተማዋ የወጣቶች የስራ አጥነት ቁጥር 18.5 ፐርሰንት መድረሱን ያመላክታል፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ቴሌቭዥን አንድ ጋዜጠኛ በጅቡቲዋ ታጁራ እና ኦቦክ ወደብ ተገኝቶ በሰራው አንድ ዘገባ ለስደት እነዚህን ሁለት ወደቦች አቋርጠው ወደ የመን ለመሻገር ስደትን የህይወት መስመራቸውን ካደረጉ በአብዛኛው ማለት ይቻላል ከድሬዳዋ ስራ በማጣት የሚሰደዱ ናቸው ከባሌ እና አጎራባ ዞኖች የሚመጡት እንደተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው፡፡ የተማረውም የከተማዋ ህብረተሰብም ተገፍቶ አካባቢውን ለቆ ወደ ሌላ ቦታ ለስራ በየሀገሩ ሲንከራተት ማየት ብዙም አዲስ አይደለም፡፡
ዘጠኝ ስራ አጡ ስራ ፈጥሮ እና በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅቶ እንዳይሰራ እና ለከተማዋም ብሎም ለሀገሩ የእራሱን አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳይችል በተለምዶአዊው የአፓርታይድ ቀመር 40፡40፡20 እና በዘርፈ ብዙ የመልካም አስተዳደር ህፀፆች ሰለባ ተዳርጎ እንዲሁ በሱስ ተጠምዶ ይባዝናል፡፡ በቅርቡ እንኳን በገሀድ እንዳየነው በከተማዋ በስራ አጡ ምስኪን ሰዎች ስም ተሰርተው የተዘጋጁ የመስሪያ ቦታዎች (Sheds) ከዛሬ ነገ የመስሪያ ቦታው ይሰጠናል ብለው ሲጠብቁ ለነበሩ ጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጆች ህግን እና ፍትህን መሰረት ባደረገ መልኩ ይደርሰናል ብለው ሲጠብቁ በዚሁ በተለምዶ የ40፡40፡20 ቀመር ሊተላለፉ ሲሉ በነዋሪው ያላሰለሰ ጥረት እና ጩኸት እንዲቀሩ ተደርገዋል፡፡ የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንትርፕራይዝ ሀላፊውም በበረታባቸው ጫና ድሬ ቲዩብ ላይ ወጥተው እንዲያስተባብሉ አድርጓቸዋል፡፡ እንደዚህ አይነት ኢፍትሀዊ የሆኖ አሰራሮች ነው እንግዲህ ለዘመናት በከተማዋ ተንሰራፍተው የከተማውን ህብረተሰብ ማግኘት የሚገባውን የኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን በተገቢው መንገድ እና ፍጥነት ማግኘት ያልቻለው፡፡
ከላይ የጠቀስኳቸው ችግሮች ሊንሰራፉ የቻሉት በዚህ ህጋዊ እውቅና በሌለው የአፓርታይድ ቀመር በሆነው 40፡40፡20 መከፋፈያ ዘዴ ነው፡፡ እናም የሚከተሉት ጉዳዮች የመፍትሄ አቅጣቻዎች መሆን ይችላሉ፡፡
1) ይህ ህጋዊ እውቅና የሌለውን 40፡40፡20 የአፓርታይድ ቀመር ማስወገድ አይነተኛ መፍትሄ ነው፡፡
2) ሌላው በከተማዋ ቻርተር ላይ የተቀመጡት ግልፅ የህግ ድንጋጌዎች በአግባቡ መተግበር አለባቸው፡፡ መሻሻል የሚገባቸውን የህግ ድንጋጌዎችን ማረቅ ቢቻል፡፡
3) ሁሉም የከተማዋ ተወላጆች እና ህብረተሰብ በእኩልነት በፍትሀዊነት አለምንም አድሎ የኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጥቅሞቻቸው እንዲከበሩ መትጋት፡፡ ለዚህ መሳካትም የከተማዋ ሰዎች በተለይ በሀላፊነት ላይ ያላችሁ የመፍትሄው አካል ብትሆኑ መልካም ነው፡፡
4) ከተማዋ በዚህ ያልተገባ ቀመር ሳይሆን ትክክለኛ በሆነው እውቀትን ችሎታን እና ልምድን መሰረት በማድረግ የከተማዋ ህብረተሰብ እራሳቸውን የማስተዳደር እኩል መብት እንዲኖራቸው ማድረግ አለብን፡፡ ቀሪዎቹን መፍትሄዎች አንባቢው እንዲያክልበት ትቼዋቸዋለሁ፡፡
በነገራችን ላይ የዚህ ፅሁፍ መነሻ የሆነኝን የ40፡40፡20 ቀመር አሁን ላይ በከተማው ተወላጆች እና ህብረተሰብ በተጨማሪም ሁለቱ ድርጅቶቹ እንወክላቸዋለን በሚሉት ማህበረሰብም ዘንድ እንኳን ሳይቀር ተቀባይነት የለውም፡፡ አሁን ላይ ይህ ቀመር የሁሉም ህብረተሰብ አጀንዳ ወደ መሆን ተሸጋግሯል፡፡ ሁሉም ይህ ከፋፋይ ቀመር እንዲወገዱለት በተለያየ መንገድ ድምፁን እያሰማ ይገኛል፡፡ ለማሳያ ይሆነን ዘንድ በቀን ሰኔ 17 2010 ዓ.ም የተከበሩ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድን ለመደገፍ እና ለማመስገን በተጠራው ሰልፍ ላይ የተገኘው ጨዋው የድሬዳዋ ህብረተሰብ በግልፅ በከተማዋ የተንሰራፋውን ኢ-ፍትሀዊነት እና የ40፡40፡20 ቀመር እንዲወገድለት ድምፁን አሰምቷል፡፡
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ በቅርቡ ፍቅር መከባበርን እና መቻቻልን መሰረቷ ወዳደረገችው ድሬዳዋ ከተማ እንደሚመጡ በወሬ ደረጃ ይሰማል፡፡ እናም እነዚህን በከተማዋ የተንሰራፉት ችግሮችን ከህብረተሰቡ ጋር በሚያደርጉት ውይይት ለመፍታት ትልቅ ጥረት እንደሚያደርጉ እኛ የድሬዳዋ ልጆች ሙሉ እምነት እና ተስፋ አለን፡፡
በመደመር ድሬዳዋ የሁላችንም ናት!!!
ድሬዳዋን ለሁሉም የምትመች ማድረግ እና የድሮ መልካም ስምና ዝናዋን የመመለስ ሀላፊነት የሁላችንም ነው፡፡

The Cosmopolitan Images of the city has to be maintained as it was before.

 

Recent Discourse over the Draft Proclamation to Determine Oromia’s Special Interest in Addis Ababa

Written By. Habtamu Birhanu (LL.B, Assistant Lecturer of Law @ Dilla University)                                        It’s a continuation from Ex-Post Discussion...

In the previous post, we have tried to see some confusions that rotates around what constitutes special interest of Oromia state in Addis Ababa and other related issues. In this part also, we will continue to see some issues related with special interest of Oromia state in Addis Ababa that is going to be determined by the draft proclamation. The other part of this draft proclamation that needs special attention is art 5. This art talks about the provision of health service and say that the residents who lives in the urban and rural areas of the special zone have the right to access to health service provided by governmental hospital and other health center as anyone in the city. Let us think of something in this regard. For one thing, this article says that the residents of urban and rural area of special zone have the right to access to health service provided by government hospital and other health center. The right to access to health services as indicated in this draft proclamation limited not only to the descendants of Oromo nation rather, it includes non-Oromo descendants who resides in the area. Because art 5 of the draft proclamation simply says that the “residents” of the area which is obvious to anyone. My concern in this regard is not why other non-Oromo residents are afforded with this right. Because, having access to health service is human right and shall not be denied on any ground. There is no any legal and moral justification to deny it. Rather the issue is that how it could be special interest of Oromia state. For one thing, this draft proclamation is designed to determine special interest of Oromo descendants on Addis Ababa. Nevertheless, in the provision that talks about the right to access to health, there is indication that this right is only limited to Oromo broods in the area. Rather the provision is all-inclusive. The clear construction of the provision show that the right to access to health services in the city is to all residents of the area and not only to the pro-genies of Oromo. If the purpose is to preserve the interest of all residents in the area, it may be correct and no question at all. Nevertheless, if it is to preserve the special interest of Oromo offspring in the area, how could it be since the provision is all-inclusive? Bear in mind that again the question is not why this right includes all residents including non-Oromo residents, rather how could it be the special interest of Oromo. The other issue in this regard is that the right to access to health service provided in the city is limited only to governmental health center. It does not indicate private one. What do you think the fate of this right as far as private health centers is concerned? Does this indicate that they have no the right to access to private health centers? If this the case, how do you see the right to access health service provided by government or private organs as recognized in different international human right instruments to some of which Ethiopia is party. For the other things, how the right access to health service is special interest? For instance article 25 of UDHR to which Ethiopia is party, clearly provides that “everyone has the right to a standard of living adequate for health and well-being of himself and his family…………and medical care…” The right to health is again recognized in ICESCR. Moreover, this covenant under its Art 12 imposes obligation on the state party to recognize the enjoyment of the highest attainable standards of physical and mental health and to take necessary step to achieve the full realization of this right to the extent the resource of the country permit. Various international and regional human right instruments also recognized this right. One interesting thing at this juncture is that Ethiopia ratified many of these human right instruments and they have force of application in Ethiopia. (Read art 9(4) and art 13(2) of FDRE constitution). With the same tone of speech, FDRE constitution under art 90(1) imposes obligation on Federal and regional governments (read art 85(2)) to design the policies that shall aim to provide all Ethiopians access to public health ………..to the extent the country’s resources permit. The reading of the above various legal provisions and discussion display for us two important things. One, the right to have access to health is human right. Nothing in different international and regional human right instruments including FDRE constitution indicates that right to health is special interest. Rather, all these human right instruments recognized it as human right. The other important messages of these human right instruments and discussion is that it is of the governments obligation to recognizes this right and takes necessary step to achieve the full realization of this right. This obligation is imposed on Ethiopian government via ratified international human right instruments and art 90(1) of FDRE constitution. In nutshell, the forgoing discussion show that the right to access to health service is human right and not special interest as designed to be determined by draft proclamation. Thus, let alone Oromo nationals who has special interest in Addis Ababa city, even non-Oromo national have right even in the other part of the country without any discrimination. So how this could be special interest of Oromia? Do we have legal and moral justification to say that? To the best of my understanding, we do not have any legal and moral justification to claim in such a way.

                                                           …to be continued.

N.B. This writing is personal opinion and is open for discussion and comment.

Recent Discourse over the Draft Proclamation to Determine Oromia’s Special Interest in Addis Ababa

Written By. Habtamu Birhanu (LL.B, Assistant Lecturer of Law @ Dilla University)

Recently Ethiopian government is going to enact proclamation that determine special interest of Oromia in Addis Ababa.

Nevertheless, this draft law from the very enactment faced confrontation and challenges from different individuals and stakeholders. I myself personally feel doubt as to what special interest of Oromia this proclamation going to determine.
Art 49(5) of FDRE constitution by taking the fact that Addis Ababa is located at the center of Oromia, provides that, special interest of state Oromia as far as provision of social services, or utilization natural resources and other similar matter as well as joint administration is concerned shall be respected.

One may ask here that what special interest constitution refer. In this regard, constitution itself has no answer. Stated otherwise, it does not define what special interest mean? Or what constitute special interest. When and how do this special interest to be implemented. It simply list down the area up on which state of Oromia has special interest. What we must take into consideration is that the lists are not open-ended. In other word they illustrative. As per the phrasing of the constitution, there are some area of special interest apart from the listed one. Constitution in this aspect left open door so that the aforementioned question and related issues to be determined by law.

After long years of panting of this special interest, draft proclamation is currently on the process to determine this special interest of Oromia in Addis Ababa. The question in this regard is that does what the constitution phrased as special interests are really special interest or rights? After all, if they are interest, what make them special interest or if not, why they are coined as special interest?
Below are some reflection on the draft proclamation whether what draft proclamation derives from the constitutional provision as special interest are really special interest or not.
Let us fist start from the definition part of the draft proclamation itself.
Like that of the constitution, draft proclamation does not define what special interest is. It simply reiterate what is already provided in the constitution. Under its art 2(4), it says that special interest mean the one that is recognized by the constitution such as provision of social services, or utilization natural resources and other similar matter as well as joint administration. Nothing is new in this draft proclamation as far as what special interest is concerned. Bear in mind that these are not special interest; rather they are the area up on which state of Oromia has special interests.
The other issue in the definition part is art 2(5). This part says, “Descendant of Oromo means it includes all the residents of Addis Ababa and peri-of the city. As far as the peri- of the city is concerned, art 2(7) of the draft proclamation says that, peri of the city means special zone around Addis Ababa. Thus, as per this draft proclamation the descendant of Oromo’s are those who are the residents of Addis Ababa and of special zone around Addis Ababa. What about others who resides far from the city like Borana, Guji……… and the like. Do you think they are not the descendants of Oromo? What do you the impact of this definition?

At least theoretically speaking, let me discuss it below.

First, let us step to the content of the draft proclamation.

The first content of the draft proclamation talks about the provision of social services. Under its sub part it say that “in the city administration, by cost of city administration, there shall be school in which the descendant of Oromo nation may learn by their language of Afan Oromo”. Interestingly, one may simply pose two easy questions. These are:

  1. Does learning by one’s own language is special interest or fundamental right.
  2. Who are the descendants of Oromo nation have the right learn in Afan Oromo in the city administration?

As far as the first question is concerned, to my best knowledge, learning by one’s own language is not special interest rather, it fundamental right. In this regard, leave alone international human right instruments our country ratified, the constitution itself under art 39(2) clearly stipulate that “Every Nation, Nationality and People in Ethiopia has the right to speak, to write and to develop its own language; to express, to develop and to promote its culture; and to preserve its history”. The concern in this regard is that, does the right to develop one’s own language bear fruit without learning by that language. Promoting and developing one’s own language presuppose learning by that language. Thus, making the language the instructional language is the soul of the right to develop one’s own language that is fundamental one. Since, Oromo nation is one of the holder of this right I didn’t see any legal and moral justification that make this special interest.

As far as the second question is concerned we have already seen that the descents of Oromo are the one who lives in the city and special zone of the city as per art 2(4) and (7) of the draft proclamation. Thus, it is only the residents of the city and special zone have the right to learn in Affan Oromo schools to be opened. Because, art 4 of the draft proclamation says that the descendants of Oromo (those who live in the city and special zone) has the right to learn in Affan Oromo School to be opened in the city by Affan Oromo. What any lay man who read this provision grasp? Theoretically speaking does this article empowered the descendants of Oromo lives far from the city and special zone?

                                          ………….to be continued.

N.B this writing is personal opinion and is open for discussion and comment.

 

The Bundle of Nihilist

Since the last plenty of years, some nihilist bloggers, cadres, bandits and other remnants have fiercely been striving a lot to deny each and every incidents of truthful tyranny of what have been happening in our country like Ethiopia. They are born without having a good temperament about their country. Bastardization of politics is their ultimate gloomy tactics in order to create a conflict among the people who have a long historically togetherness and cooperation’s. Nihilists, in whatever circumstances and positions they are, uses their intellectual efforts against the existence of state. This is to mean that the bundle of nihilist don’t want to maintain the unity of the country and they don’t have any experience of bringing people together.  As my little puppy, frequently exhaust their time for sniffing the fleshy differences of our people. If people are living together by tolerating their differences, they could become anger and disappointed. Nothing better than conflict and discontent for the nihilist. Ethiopians are in need of national peace, unity and consensus even though they have been baring for the nihilist veiled and disgusted agendas.

Most significantly, there is a brand motto that consolidate the existence of Ethiopia as a state and maintain the braveness of its people i.e. “United we stand, divided we fall”. Please, our brothers and sisters, more than ever, we need to maintain our unity and stand together by avoiding those microbes (Nihilist) from our body.

Continue reading “The Bundle of Nihilist”

ETHIOPIA IS UNDER SEVERE TRAUMA

 

Since the last plenty of 25 years, we Ethiopians are under a chronic poverty and misery. What make things so worth because we are leading our life with a tyrannical regime. This tyrannical regime is highly engaged in suppressing the people’s grievance and voices unreasonably. The regime reacted for the people’s grievances by using a barrel of gun and his troops and intelligence officials. We know perfectly that EPRDF came to power by a violent struggle and at the earliest stage of their power the regime promised and pledged to the people of Ethiopia to realize democracy, freedom, justice, development and so forth. But today they expressly broke what they have promised to the people of Ethiopia.

Poverty, lack of good governance, democratic institution alien for the concept of democracy, no development, lack of good social amenities and welfare’s, no freedom  of expression, income inequality, corruption, oppression, mass killing, instability, lack of trust on the existing government and etc are the most prevalent and rampant problems in Ethiopia right now. Peoples are yet shouting their voices even by marching to the street and even by making a large rally on the street. The government has failure to address the peoples questions at hand rather the government is highly exhausts it’s time to shut up the peoples mouth by his troops and militias.

Since the Oromo’s made a first mass protest and rally on the master plan of Addis Ababa, still there is a mass protests and rally against the regimes across the country regarding different issues. There is a mass protest in Gonder with respect to Kemant and Wolkaite-Tegede self-rule or self administration questions. The same questions are yet raised in SNNPR regional states, Konso’s self-administration question. In oromia yet a number of peoples are yet spends their time on the street to oppose government’s mass killings against the innocent Oromo’s individual. The government does not have a commitment and willing to avert the problems so far rather than shooting the peoples by a gun illegally at the expense of sustaining its power. Since the last plenty of months many innocent individuals across the country have been killed, wounded fatally and lose their body by the regime’s forces unlawfully. Many of them are yet throwing to jail in the name of fabricated terrorism crime.

Hence, we Ethiopians, as a citizen we should have to strive a lot to discuss and make a deliberation on the issues as well in order to protect Ethiopia from disintegration and so as to protect the peoples from mass government killings and oppression. Even the tyrannical regime should have to take a political commitment to create a national consensus among the whole peoples of Ethiopia. we should have to take a lesson from the then regime’s horrific acts and measures.